Telegram Group & Telegram Channel
Forwarded from Mizan tube (Abdi Ikhlas)
#እንዴት_ታሰርን? – #ኢኽላስ_ጀመዓ

ማክሰኞ እለት ነበር ለመውሊድ ያዘጋጀነውን መንዙማ በቪድዮ ለመሰራት ከጀመዓችን የሴት አባላት የአንዷ አባል እህት ቤት የተገኘነው።

ገና ቀረፃውን ከመጀመራችን ሲቪል እና ዩኒፎርም የለበሱ ፖሊሶች ተከታትለው ገቡ። ግቢ ውስጥ ስለነበር እየቀረፅን የነበረው እንደገቡ አገኙን እኛ እየሰራን የነበረው ሰላማዊ ስራ ስለነበር ቀለል አርገን ተመልክተነው ነበር።

እነሱም ቀለል ባለ ስሜት እያዋዙ ካሜራ እንድናጠፋ ካዘዙን በኋላ ለናንተው ሲባል ነው ፖሊስ ጣብያ ደርሰን ለፎርማሊቲው (ለደንቡ) ሰላማዊ መሆናችሁን ፈርማችሁ ትወጣላችሁ ብለው እኛንም ካሜራ ማኖቻችንንም ይዘውን ሄዱ።

ፖሊስ ጣብያው እንደደረስን እስከ 10 ሰዓት ቁጭ ካረጉን በኋላ ቃል ስጡ አሉን። ቃል ስንሰጥ የተጠረጠርንበት ክስ ይነበብልን ጀመር ያኔ ነው የደነገጥነው እንዴት 1 ሰው ሙስሊም መሆኑ ብቻ አክራሪ ወንጀለኛ ተብሎ ያስከስሰዋል?

ብቻ የሆነው ሆኖ ወደ መምሸት ተቃርቦ 12 ሰዓት ሲሆን ያልጠበቅነው ዱብዳ ወረደ እሱም የጫማ ክር እና ቀበቶ ፍቱ ተባልን ስልካችን ተወሰደና አንዲት ጠባብ ጨለማ ቤት ውስጥ ወረወሩን። በጣም ያስፈራ በጣም ይጨንቅም ነበር ለ 5 ሰው በማይበቃ ቤት ውስጥ አስራ ዘጠኝ ሰው ላይ በላይ አነባበሩን በዛ ላይ ጨለማ። ከዛም አልፎ ለቤተሰቦቻችን ያለንበትን ሁኔታ ለማሳወቅ ስልክ አስደውሉን ብለን ብንለምን ሰሚ ጆሮ ጠፋ።

እዛች ክፍል ውስጥ ታጭቀን አደርን ግማሹ ተኝቶ ግማሹ ቁጭ ብሎ። በዛ ላይ ሽንት ሚሸናው ለሊት 11 ሰዓት እና ማታ 11 ሰዓት 2 ግዜ ብቻ ነው። በድንገት ሰምተው ሊጠይቁን የመጡ ቤተሰቦቻችንም እንዳያዩን ተደረገ።

በቀጣዩ ቀን ልክ 9 ሰዓት አከባቢ ሀይለኛ ዝናብ ላያችን ላይ እየዘነበ በፓትሮል መኪና ጭነውን ቡልቡላ ፖሊስ ጣብያ ወሰዱን።

አልሀምዱሊላህ እዛ ግን ደስ ይል ነበር ቤተሰቦቻችንን ማናገር፣ስልክ መደወል ቻልን ክፍሉም ትልቅ አዳራሽ ነበር ማብራትም አለ ፖሊሶቹም አላህ የወደዳቸው ምርጦች ነበሩ።

ቢሆንም እስር ቤት ነውና በፖሊስ እየተጠበቁ መንቀሳቀስ ከባድ ነው አቀባበላችው ማራኪ ከመሆኑም በላይ ከኛ በፊት ታስረው የነበሩትን 23 አከባቢ እስረኞች ለኛ ቦታውን አስለቅቀው የተሻለ እንክብካቤ ይደረግልን ጀመር። በዛ ላይ ካቦ (የእስረኞች አለቃ) እንደ አዲስ ይመረጥ ተብሎ እኔው ተመረጥኩ 😊

ፖሊሶቹ ለካቦ ቦታ አላቸው በቃ ገብቼ ማላውቀውን እስር ቤት እንደ ለማዳ ታሳሪ ስመራዉ ቆየሁ መሸና ለያንዳንዳችን አንዳንድ ፍራሽ ተሰጥቶን ተመቻችተን አደርን።

በዚህ መሀከል ወደ ደጅ ስንዞር እኛን ለመጠየቅ የመጣው ሰው ወላሂ አጀብ ያሰኛል። ኢኽላስ እውነትም ሰው አለው እንድል አደረገን። ያውም ቁርጡ ሳይታወቅ ለማንም አይነገር ተብሎ እስክንፈታ ድረስ በይፋ ለማንም አልተነገረም ነበር። በአላህ እዝነት በብዙዎች ዱአ በብዙዎች ሩጫና ልፋት መስዋትነት ተከፍሎበት ሀሙስ 9:30 ከእስር ተፈታን።

ውስጥ ባለንበት ሰዓት እንደ ጉድ አሽቀናል ቂሳ እና እስቲግፋር በጋራ ተዋውሰናል ልዩ ትዝታ ልባችን ላይ አትመናል። ክፉና ደጉን ተመልክተናል የቁርጥ ቀን ወዳጃችንንም አይተናል። በዚህ አጋጣሚ ለሊት 12 ሰዓት እየማጣችሁ ቁርስ ምሳ እራት ቡልቡላ ድረስ እያመጣችሁ የእስር ቤቱን ምግብ እንዳንበላ ለካደማችሁን የኢኽላስ ጀመዓ ያልታሰራችሁ ወንድ እና ሴት አባሎቻችን ጓደኞች እና ሌሎች በኛ ጉዳይ የተንከራተታችሁ በሙሉ እኛ አቅም የለንም አላህ ኸይር ጀዛቹን ይክፈል ውዶቼ።

አሁንም የምንለው በዲናችን ምክንያት መታሰር ይብቃን እና ኡስታዛችን ኡስታዝ ፈድሉም እንደኛ ይፈቱልን። እኛ በተፈጠረው ሁሉ ኮራን እንጂ አልተቆጨንም።

ለሌሎች ትምህርት እንሆን ዘንድ ሁላችሁም ራሳችሁን ጠብቁ። አክራሪ አይደለንም እኛ ሙስሊሞች ነን። አልሀምዱሊላህ አላ ኩሊ ሀሊን። 🙏🙏🙏🙏

አብዲ ኢኽላስ

👉 @IkhlassTube

tg-me.com/Ineiyalehucharity/623
Create:
Last Update:

BY እኔ እያለሁ የመረዳጃ ተቋም ( Ineiyalehu )

Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 283

Share with your friend now:
tg-me.com/Ineiyalehucharity/623

View MORE
Open in Telegram

እኔ እያለሁ የመረዳጃ ተቋም Ineiyalehu Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

Telegram announces Search Filters

With the help of the Search Filters option, users can now filter search results by type. They can do that by using the new tabs: Media, Links, Files and others. Searches can be done based on the particular time period like by typing in the date or even “Yesterday”. If users type in the name of a person, group, channel or bot, an extra filter will be applied to the searches.

Telegram and Signal Havens for Right-Wing Extremists

Since the violent storming of Capitol Hill and subsequent ban of former U.S. President Donald Trump from Facebook and Twitter, the removal of Parler from Amazon’s servers, and the de-platforming of incendiary right-wing content, messaging services Telegram and Signal have seen a deluge of new users. In January alone, Telegram reported 90 million new accounts. Its founder, Pavel Durov, described this as “the largest digital migration in human history.” Signal reportedly doubled its user base to 40 million people and became the most downloaded app in 70 countries. The two services rely on encryption to protect the privacy of user communication, which has made them popular with protesters seeking to conceal their identities against repressive governments in places like Belarus, Hong Kong, and Iran. But the same encryption technology has also made them a favored communication tool for criminals and terrorist groups, including al Qaeda and the Islamic State.

እኔ እያለሁ የመረዳጃ ተቋም Ineiyalehu from ua

Telegram እኔ እያለሁ የመረዳጃ ተቋም ( Ineiyalehu )
FROM USA